tag:blogger.com,1999:blog-232019842009-02-20T18:46:18.946-08:00ECTV AMHARIC NEWSectvnoreply@blogger.comBlogger6125tag:blogger.com,1999:blog-23201984.post-1157846739311276672006-09-09T17:05:00.000-07:002006-09-09T17:05:39.313-07:00የእንቁጣጣሽ በዓል ሲከበር ለሚሊኒየሙ በዓል አከባበርም ዝግጅት እንዲደረግ ተጠየቀአዲስ አበባ ጳጉሜን 4/1998/ዋኢማ/ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ አዲሱን የ1999 ዓ.ም. የእንቁጣጣሽ በዓል ሲያከብር ብቸኛ የጥቁር ህዝቦች በዓል የሆነውና በ2000 ለሚከበረው የምዕተ ዓመቱ የኢትዮጵያ በዓልም ዝግጅት እንዲጀምር የኢትዮጵያ ሚሊኒየም በዓል አከባበር ምክር ቤት ጠየቀ።

የምክር ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስዩም በረደድ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት፤በኢትዮጵያ ሚሊኒየም ህዝቡ ወጉን፣ልማዱን፣ባህሉንና ቅርሱን እንዲሁም ምርቱንና መልካም ገጽታውን ለዓለም ለማስተዋወቅ ከወዲሁ መዘጋጀት አለበት።

ከብሄራዊ ምክር ቤቱ አላማዎች መካከል እያንዳንዱ ዜጋ በ2000 ዓ.ም ሁለት ችግኞችን እንዲተክል ማድረግ እንደሚገኝበትና በሀገሪቱ ውስጥ በሚገኙ ትልልቅ ከተሞች በእያንዳንዳቸው ሁለት ሺ ዛፎችን በመትከል አንድ የሚሊኒዮም ፓርክ ለማቋቋም መታሰቡን አቶ ስዩም ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ 2000ን በሙሉ በሚከበረው በዓል ህዝቡ የባህል ልብሶችን፣ቋንቋዎችንና ዳንሱን ፣ታሪኩንና ቅርሶቹን ከማስተዋወቅ ባሻገር የጋራ አገራዊ ራዕይና አመለካከት ለመፍጠርና ገቢውን ለማሳደግ በሚያመቸው አደረጃጀት ዝግጅቱን እንዲጀምር ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ምዕተ ዓመት በአል በሚከበርበት ዓመት የሀረር ከተማ አንደ ሺ ዓመት በዓል እንደሚከበር ተናግረው፤በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጥበብ ትምህርት ክፍልም 50ኛ ዓመት የልደት በዓሉን የሚያከብርበት በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ 2000 ሚሊኒየም በዓል ብቸኛ የጥቁር ህዝብ በዓል በመሆኑ አፍሪካዊያን ወንድሞቻችንም ተካፋይ የሚሆኑበት ሁኔታ እየተመቻቸ እንደሚገኝ ጨምረው አስረድተዋል።

ለበዓሉ አከባበር መንግስት የሰጠው ትኩረት ከፍተኛ በመሆኑ የተሟላ ፅህፈት ቤት አደራጅቶ ስራ የጀመረው ምክት ቤት የራሱን ድረ ገፅ በቅርቡ ይፋ በማድረግ በዓለምአቀፍ ደረጃ ስራውን እንደሚያፋጥን አቶ ስዩም አስታውቀዋል።

ለሚሊኒየም በዓል አከባበሩ ሁሉም ወገኖች አገራዊ ራዕይና በመፍጠር የጋራ ጥረት እንዲጀምሩና የመገናኛ ብዙሃንም ለምክር ቤቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ሲል ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።
Amharic News From ECTV
ectvnoreply@blogger.com0tag:blogger.com,1999:blog-23201984.post-1157841707250368702006-09-09T15:41:00.000-07:002006-09-09T16:46:46.653-07:00ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወደ ሊቢያ ሔዱአዲስ አበባ, ጳጉሜን 4 ቀን 1999- ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአፍሪካ ሕብረት የታወጀበት ሰባተኛ ዓመት በዓል ላይ ለመገኘት ትናንት ወደ ሊቢያ መጓዛቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ወደ ሊቢያ የተጓዙት የአገሪቱ መሪ ኮሎኔል ሙአመር አል ጋዳፊ በበዓሉ ላይ እንዲገኙ ባደረጉላቸው ጥሪ መሠረት ነው፡፡ የአፍሪካ ሕብረትን ለመመሥረት በአፍሪካ አገሮች መሪዎች መካከል የተደረሰው ስምምነት የታወጀው በሊቢያ የሰርት ከተማ እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር መስከረም 9 ቀን 1999 ነበር፡፡
Amharic News From ECTV
ectvnoreply@blogger.com0tag:blogger.com,1999:blog-23201984.post-1157841459016194672006-09-09T15:36:00.000-07:002006-09-09T15:37:39.033-07:00የዓረብ ሊግ ከኢጋድ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚኖርበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀአዲስ አበባ ጳጉሜን 3/13/ 1998

በሶማሊያ የሰላም ጉዳይ ላይ ማደራደር የሚፈልግ ማንኛውም አካል ከኢጋድ ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚኖርበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ኢጋድ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የዓረብ ሊግን ሙሉ በሙሉ እያሳተፈ እንደቆየ ሁሉ ሊጉም በተመሳሳይ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት ገልጿል።

ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በናይሮቢና በካርቱም በሶማሊያ ጉዳይ ላይ የተካሄዱ ስብሰባዎችን አስመልክቶ ለሚኒስቴሩ የፕሬስ ኢንፎርሜሽንና ዶክመንቴሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ላቀረበው ጥያቄ በሰጠው ምላሽ የተሻለውና ተመራጩ አካሄድ በሶማሊያ ጉዳይ ማደራደር የሚፈልግ ወገን ከኢጋድ ጋር መተባበርና መቀናጀት ይገባዋል ብሏል።

በናይሮቢ የኢጋድ ስብሰባ በሚካሄድበት እለት በተመሣሣይ በአረብ ሊግ አደራዳሪነት በካርቱም በሶማሊያ የሽግግር መንግስትና በእስላማዊ ፍርድ ቤቶች ህብረት መካከል ውይይቱ ቀጥሎ እንደነበር ገልጾ ሁለቱ ስብሰባዎች ተደጋጋፊ እንደነበሩም አስታውቋል።

የካርቱሙ የስምምነት ይዘት የሁለቱን ተቃራኒ ወገኖች ሚሊሺያና ሰራዊት ወደፊት በሚደረስ ስምምነት ማዋሃድ፣ በሌላ ጎረቤት አገር ላይ ትንኮሳ አለማድረግ፣ የተሸነፉ የአንጃ መሪዎች እንዳያንሰራሩ ማድረግና ለሶማሊያ ህዝብ ፍላጐት ተገዥ መሆን ይገባል የሚል ውሳኔዎች ማሳለፉን ገልጿል።

በተጨማሪ በእንጥልጥል ላይ ያሉት የፖለቲካ የጸጥታና የስልጣን ክፍፍል በቀጣዩ ውይይት እንዲታይ የሚሉ ውሳኔዎች በበጐ መልኩ የሚታዩና ኢትዮጵያ የምትደግፋቸው እንደሆኑ አመልክቷል፡፡

ሆኖም ግን የአረብ ሊግ በካርቱሙ ስብሰባ ላይ ኢጋድን በታዛቢነት እንዲቀመጥ የሚል ውሳኔ ማሳለፉ ለኢጋድ ልፋትና ጥረት ተገቢ ዋጋ ባለመሆኑ ኢትዮጵያም ሆነች አባል አገራቱ የማይደግፉት እንደሆነ አስረድቷል፡፡

የሶማሊያ ጉዳይ በኢጋድ ብቻ ይታይ የሚል ዕምነት በኢትዮጵያም ሆነ በኢጋድ በኩል የለም ያለው ዳይሬክቶሬቱ ኢጋድ የሶማሊያን የሰላም ጉዳይ ከስድስት ዓመታት በፊት ጀምሮ በበላይነት እየመራ ለዚህ ደረጃ ያደረሰ ስለሆነ የአረብ ሊግ አደራዳሪነት እንደተጠበቀ ሆኖ ኢጋድም በዚህ መድረክ ሙሉ ተሳታፊ መሆን እንደሚኖርበት ያምናል ብሏል።

ኢጋድ በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የዓረብ ሊግን ሙሉ በሙሉ እያሳተፈ እንደቆየ ሁሉ ሊጉም በተመሳሳይ መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅበት ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል።

የኢጋድ አባል አገራት በናይሮቢ ስብሰባቸው የሠላም አስከባሪ ኃይል ወደ ሶማሊያ በመግባት ለሽግግር መንግስቱ የጦር ሠራዊት፤ የደህንነትና የፖሊስ አባላት ስልጠናና ድጋፎችን እንዲሠጥ ከስምምነት ላይ መደረሱን ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል፡፡

ኢጋድ የሠላም አስከባሪ ወደ አካባቢው እንዲገባ የወሰነው በአገሪቱ ሠላምንና መረጋጋትን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት ይበልጥ ለማገዝ ያስችላል ብሎ በማመኑ ነው ያለው ዳይሬክቶሬቱ ኢትዮጵያም እንደ ኢጋድ አባልነቷና ውሳኔውን መደገፏን አስታውቋል፡፡

በተጨማሪ የኢጋድ አባል አገራቱ በናይሮቢ ስብሰባቸው የሶማሊያ የፌዴራል የሽግግር መንግስቱን ተቋማት ለማጠናከር መወሰናቸውን ዳይሬክቶሬቱ አመልክቷል፡፡

ቀደም ሲል ኢጋድ በተለያዩ መድረኮች በሶማሊያ ጉዳይ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኤርትራ መንግሰት እንደ አንድ አባል አገር አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም በተቃራኒው አክሪሪውን ቡድን በሕቡዕ ሲያግዝ መቆየቱን አስታውቋል፡፡

በኢጋድ የመከላከያ ኢታማዦር ሹሞች እና በአፍሪካ ህብረት የፀጥታ ምክር ቤት በተላለፈው ውሳኔ መሰረት በሶማሊያ ላይ የተጣለው የጦር መሣሪያ ማእቀብ የማንሳት ጥያቄ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት እንዲተላለፍ መደረጉንም አስረድቷል፡፡

የኤርትራ መንግስት በየጊዜው በሚያራምደዉ ተለዋዋጭ አቋሙ ምክንያት ለሶማሊያ ሕዝብ እና ለቀጠናው ሠላም ያለውን ደንታ ቢስነት አረጋግጧል ያለው ዳይሬክቶሬቱ የሻዕቢያ መንግስት በድንበር አሳቦ የኢትዮጵያን ሃብት ለመመዝበር ባለመቻሉ የአገሪቷን ሠላም ለማወክ በከንቱ እየለፋ ይገኛል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ለሠላም የሚደረጉ ስምምነቶችን በሙሉ እንደሚደግፍ ዋና ዳይሬክቶሬቱ ጠቁሞ አገራችን እስከ አሁን ድረስ ስታደርግ የነበረውን ጥረት ለወደፊቱም አጠናክራ እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለፁን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡
Amharic News From ECTV
ectvnoreply@blogger.com0tag:blogger.com,1999:blog-23201984.post-1142870334430889962006-03-20T07:58:00.000-08:002006-03-20T07:58:54.443-08:00ኅብረተሰቡ ያለሥጋት ዶሮ አብስሎ የመመገብ ባህሉን መቀጠል እንዳለበት ተገለፀአዲስ አበባ መጋቢት 11/1998/ዋኢማ/ ኅብረተሰቡ ሳይሰጋና ሳይደናገር ዶሮ አብስሎ የመመገብና የማርባት ባህሉን መቀጠል እንዳለበት ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።የወፍ ጉንፋን በሽታ በሀገራችን ቢከሰት እንኳን ኢንስቲትዩቱ ክትባቱን የማምረት አቅም እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶክተር በርሄ ገብረእግዚአብሔር ዛሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል እንደገለፁት ህብረተሰቡ ዶሮም ሆነ እንቁላል አብስሎ የመመገብና ዶሮ የማርባት ባህሉን ያለ ሥጋት መቀጠል አለበት፡፡

በኢትዮጵያ በሽታው አለመኖሩ እንደተረጋገጠና ኢንስቲትዩቱ መንግስት ካቋቋመው ግብረ ሃይል ጋር ጉዳዩን አስመልክቶ በዓለም ላይ ያሉ መረጃዎችን በመከታተልና ቅኝት በማድረግ በትጋት እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ኅብረተሰቡ ዶሮና የዶሮ ተዋጽዖዎችን አብስሎ የመመገብ ባህሉን ማዳበሩ ለዚህ በሽታ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ተዛማች በሽታዎች የጎላ ጠቀሜታ ስላለው አዳብሮ መቀጠል አለበት፡፡

የወፍ ጉንፋን በሽታ ከሌሎች ተመሳሳይ በሽታዎች የሚለየው ከእንስሳት ወደ ሰው የመተላለፉ አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ ነው ያሉት ዶክተር በርሄ፤ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችለውን ክትባት ትክክለኛ ዝርያ ከዓለም አቀፍ ሪፈራል ላቦራቶሪዎች በማስመጣት በሀገራችን ማምረት እንደሚቻል አስረድተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ክትባቱን ለማምረት ያለው ቴክኖሎጂ አሁን በዓለም ላይ ካሉት ቴክኖሎጂዎች ብዙ ያልተራራቀ ስለሆነና ከወፍ ጉንፋን በሽታ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ክትባቶች የማምረት ልምድ ስላለው ሊፈጠር የሚችልን ችግር የመፍታት አቅም እንዳለው አስታውቀዋል፡፡

ኀብረተሰቡ ከዚህ በፊት ስለጉዳዩ ከባለሙያዎች የተላለፉትን መረጃዎች ተከትሎ ያደረገው ጥንቃቄ ተገቢ እንደነበር ጠቅሰው፤በባለሙያዎች በተደረገው ግምገማ በሽታው በሀገራችን ባለመከሰቱ ዶሮና እንቁላል አብስሎ የመመገብ ባህሉን አዳብሮ በመቀጠል፣ ስለበሽታው ከባለሙያዎች በየጊዜው የሚተላለፈውን መልክት በንቃት መከታተል እንዳለበትም ዳይሬክተሩ አሳስበዋል።

ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት ከተቋቋመ 42 ዓመታትን ያስቆጠረና ከ16 በላይ የእንስሳት በሽታ ክትባቶችን በማምረት ላይ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ከዶክተር በርሄ ገለፃ ለመረዳት መቻሉን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል፡፡
Amharic News From ECTV
ectvnoreply@blogger.com0tag:blogger.com,1999:blog-23201984.post-1142655725501101362006-03-17T20:21:00.000-08:002006-03-17T20:22:05.513-08:00ፕሬዚዳንቱ በትግራይ ክልል የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ መቀሌ ገቡፕሬዚዳንቱ በትግራይ ክልል የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ መቀሌ ገቡ
መቀሌ መጋቢት 8/1998/ዋኢማ/ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በትግራይ ክልል ለአንድ ሣምንት ያህል የሥራ ጉብኝት ለማድረግ መቀሌ ከተማ ገቡ ።

ፕሬዚዳንት ግርማ ለስድስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ከሰዓት በፊት በመቀሌ አሉላ አባነጋ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ጸጋይ በርሄ ፣የክልሉ መንግሥት ካቢኔ አባላት፣የሃይማኖት መሪዎችና የከተማው ነዋሪ ተወካዮች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ።

ፕሬዚዳንቱ በቆይታቸው በኩይሃ የተገነባውን የስጋ ደዌ ህክምና ዘመናዊ ሆስፒታል በነገው ዕለት እንደሚመርቁና በ3 ቢልየን ብር በሚጠጋ በጀት እየተገነባ ያለውን የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት እንደሚጎበኙ ታውቋል።

ፕሬዚዳንት ግርማ በተጨማሪም በሼህ መሀመድ አላሙዲ የተገነባውን ማጋርመንት የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ እንደሚመለከቱና እንዲሁም ከክልሉ አገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ከወጣው ፕሮግራም ለማወቅ ተችሏል ሲል ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል ።
Amharic News From ECTV
ectvnoreply@blogger.com0tag:blogger.com,1999:blog-23201984.post-1141192422112561542006-02-28T21:52:00.000-08:002006-02-28T21:53:42.126-08:00ዩኒኮድ ምንድን ነው?ዩኒኮድ ምንድን ነው?
ዩኒኮድ ለእያንዳንዱ ፊደል፣
ማንኛውም ዓይነት ኮምፒውተር ቢሆን፣
ማንኛውም ዓይነት ፕሮግራም ቢሆን፣
ማንኛውም ዓይነት ቋንቋ ቢሆን፣
ልዩ የሆነ ቍጥር ያዘጋጃል።

በመሠረቱ ኮምፖውተሮች የሚሠሩት ከቍጥሮች ጋር ነው። ለእያንዳንዱ ፊደል ቍጥሮችን በመመዝገብ ፊደሎችንና ሌሎች አሃዞችን ይመድባሉ። ዩኒኮድ ከመፈልሰፉ በፊት እነዚህን ቍጥሮች ለመሰየም በመቶ የሚቆጠሩ የተለያዩ የስያሜ አፈታት ዘዴዎች ነበሩ። ይህም ማለት አንድ የተወሠነን ስያሜን ለመፍታት ብዙ አሃዞችን ያካተተ አልነበረም። ለምሳሌ የአውሮፓ ኅብረትን ብንወስድ ሁሉንም ቋንቋዎቹን ለመሸፈን ብዙና የተለያዩ የአፈታት ዘዴዎች ያስፈልግ ነበር። ለእንግሊዘኛ ቋንቋ እንኳን አንድ ብቸኛ የአፈታት ዘዴ ለሁሉም ፊደሎች፣ ሥርዓተ ነጥቦችና ምልክቶች በጋራ ለመጠቀም በቂ አልነበረም።

እነዚህ የስያሜ አፈታት ዘዴዎች እርስ በእርሳቸው የሚቃረኑበትም ጊዜ አለ። ይህም የሚሆነው ሁለት የአፈታት ዘዴዎች ለተለያዩ ፊደላት አንድ ዓይነት ቍጥር በሚጠቀሙበት ጊዜ ወይንም ደግሞ የተለያዩ ቍጥሮችን ለአንድ ፊደል በሚጠቀሙበት ጊዜ ነው። ማንኛውም ኮምፒውተር በተለይ አስተናጋጆች የተለያዩና ብዙየአፈታት ዘዴዎችን መደገፍ ያስፈልጋቸዋል። ግን በተለያዩ የአፈታት ዘዴዎች ወይም ኮምፒውተሮች መሀል መረጃ በሚተላለፍበት በማንኛውም ጊዜ የመዘበራረቅ አደጋ ሊከሰት ይችላል።

ዩኒኮድ ይህን ሁሉ ለውጦታል

ዩኒኮድ ለማንኛውም ኮምፒውተር፣ ለማንኛውም ፕሮግራምና ለማንኛውም ቋንቋ ለእያንዳንዱ ፊደልተፈላጊውን ልዩ የሆነ ቍጥር ያቀርባል። የዩኒኮድን የአሠራር ዘዴ በአሁኑ ጊዜ በታወቁት ታላላቅ መሪ ኢንዱስትሪዎች እንደ Apple, HP, IBM, JustSystem, Microsoft, Oracle, SAP, SUN, Sybase, Unisys, እና በሌሎችም ዘንድ ጥቅም ላይ እየዋለ ነው። ዩኒኮድ እንደ XML, Java, ECMAScript (JavaScript), LDAP, CORBA 3.0, WML, ወዘተ ባሉ ወቅታዊ ደረጃቸውን በሚጠብቁ ዘንድ ተፈላጊነት ያለው ሲሆን ISO/IEC 10646ን በሕጋዊ መልኩ ጥቅም ላይ የሚያውልበት ነው። ዩኒኮድ በብዙ የኮምፒውተር መምሪያ ፕሮግራሞች፣ ማንኛቸውም አዳዲስ የድረገጽ መመልከቻ ፕሮግራሞች እና እንዲሁም የተለያዩ ፕሮግራሞች የሚደግፉት ነው። ዩኒኮድ በተለያዩ የአሠራር ዘዬዎች፣ ተጨማሪ ፕሮግራሞች፣ ድረገጾች እና በሌሎችም ምርቶች የተደገፈ ነው። የዩኒኮድ ስታንዳርድ ብቅ ማለቱ እና ለሱ ድጋፍ የሚሰጡ መሣሪያዎች መቅረባቸው በዘመኑ ከተፈጠሩት አለማቀፋዊ የሶፍትዌር የቴክኖሎጂ ክስተቶች ዋናዎቹ ናቸው።

ዩኒኮድ በኔትወርክ በሚሰሩ ኮምፒውተሮች እና ድረገጾች ጋር በማቀናጀት በዋጋ በኩል ታላቅ የወጪ ቅናሽ ይሰጣል። አንድን የሶፍትዌር ምርት ወይንም አንድን ድረገጽ ለተግባረ ብዙ ኮምፒውተሮች፣ ቋንቋዎችና ሀገሮች እንደገና ማስተካከል ሳያስፈልግ ተግባር ላይ ማዋል ይችላል። መረጃዎቹን ምንም እንከን ሳያጋጥማቸው በልዩ ልዩ የአሠራር ዘዴዎች እንዲንሸራሸሩ ያደርጋል።

የዩኒኮድ ጉባኤ

የዩኒኮድ ጉባኤ አትራፊ ድርጅት ሳይሆን የተመሠረተው የዩኒኮድን ደረጃ ለማሣደግ፣ ለማስፋፋት እና በተግባር ላይ እንዲውል ለማድረግ ነው። ዩኒኮድ የፅሑፍን አቀራረብ በወቅታዊ ሶፍትዌር ውጤቶችና ደረጃዎች ይደነግጋል። የጉባኤው አባልነት ሰፋ ያለ የኮምፒውተርና ከኮምፒውተር ጋር ተቀናብረው የሚሄዱ ድር ጊቶችን የሚሸፍን ትላልቅ ድርጅቶችን ያካተተ ነው። ይህ ማዕከል የሚደገፈው ከአባሎቹ በሚዋጣው ገቢ ብቻነው። በአለም ዙሪያ ላሉ የዩኒኮድን ስታንዳርድ (ደረጃ) ለሚደግፉ እና በእድገቱም ሆነ በአሠራሩ ለመርዳት ለሚፈልጉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የዩኒኮድ ጉባኤ አባልነት በር ክፍት ነው።

Amharic translation by The Ge'ez Frontier Foundation
Amharic News From ECTV
ectvnoreply@blogger.com0